የልደታ ማንፋክቸሪንግ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዳሬክቶሬት ከልደታ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት እና ከወረዳ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የአዲስ ኢንተርፕራይዝ እርክክብ እና ድጋፉን ውጤታማነትን ለማረጋገጥ በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አደረጉ።
ወ/ሮ የሺወርቅ እንየው እደተናገሩት ዛሬ በሰነድ የተረከብናቸውን ኢንተርፕራይዞችን በቀጣይ በጋራ የአካል እርክክብ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበው በቀጣይም የድጋፍ ስራችንን ውጤታማ ለማድረግ በጋራ አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል።
የልደታ ክፍለከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ተወካይ ወ/ሮ ዝናሽ ዘውዴ በበኩላቸው እንተርፕራይዞች የተለዩት ለኮሌጁ ቅርበት ያለውን ወረዳዎች ማለትም ወረዳ 1, 2, 3, 5. እና 7 ሲሆኑ ኮሌጁ የሚሰጠውንም ድጋፍ ከኮሌጁ ጋር በጋራ ሆነው የሚከታተሉ የየወረዳ ተወካይ ባለሙያዎች በመመደብ በጋራ እንድንወያይ የደረጉ በቀጣይ ለሚኖረው የመረጃ ልውውጥ ወጥ የሆነና ተናባቢ ስራ መስራት ያስችለናል ብለዋል።




.