✨ ወርቃማ ሰኞ ✨
"የስራውም ሆነ የሙያው ባለቤት እኛው ነን!"
በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ሳምንታዊ 'ወርቃማ ሰኞ' የዕውቀት ማጋራት ፕሮግራም፣ የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ምክትል ዲን የሆኑት ወ/ሮ የሺወርቅ እንየው ካካበቱት ሰፊ ልምድ በመነሳት "የሙያ ባለቤት እኛው ነን" በሚል ርዕስ አነቃቂ እና አስተማሪ መልዕክታቸውን አጋርተዋል።
በመልዕክታቸውም፣ የተቋማችን ስኬት የሚረጋገጠው እያንዳንዳችን በያዝነው የሥራ ድርሻ ላይ በምናሳየው የባለቤትነት ስሜት፣ ኃላፊነታችንን በአግባቡ በመወጣት እና በትጋት ላይ የተመሰረተ መሆኑን አስገንዝበዋል።
"የነገውን የሰው ኃይል የምንቀርፅ እኛው ነን። በዲሲፕሊን የተካኑ ቴክኒሻኖችን ከፈለግን፣ እኛ እራሳችን ዛሬ አርአያ መሆን አለብን።" - ወ/ሮ የሺወርቅ እንየው
አክለውም፣ የኮሌጁን ተልዕኮ በባለቤትነት ስንይዝ፣ ዲሲፕሊንን ስንለማመድ እና ሙያዎችን ስናከብር፣ ብቁ ቴክኒሻኖችን ብቻ ሳይሆን ኢንዱስትሪን፣ ማህበረሰብን እና ህይወትን የሚቀይሩ ባለሙያዎችን እንደምናፈራ ገልጸዋል።
ለሰጡት አነቃቂ የዕውቀት ሽግግር ወ/ሮ የሺወርቅን ከልብ እናመሰግናለን!


.