ወርቃማ ሰኞ
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
በ"ወርቃማ ሰኞ" መድረክ
የአለም-ልክ ክህሎቶች ለኢትዮጵያ ! World- class skills for Ethiopia
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) አሰልጣኝ የሆኑት አቶ አቤንኤዘር ግርማ ባቀረቡት ገለጻ፣ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ የክህሎት ስልጠናዎችን መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አሳሰቡ። "ወርቃማ ሰኞ" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ አሰልጣኝ እንዳብራሩት፣ በአሁኑ ወቅት ክህሎት ዋነኛው ገንዘብ መሆኑንና ሀገራትም የዜጎቻቸውን ክህሎት በማሳደግ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።
አሰልጣኝ አቤንኤዘር በንግግራቸው
እያንዳንዱ ወጣትና ባለሙያ ከዓለም ምርጦች ጋር በእኩል ደረጃ የሚታይበት፣ የሚወዳደርበትና በመሪነት የሚቆምበት ኢትዮጵያን ማለም አለብን
ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ይህንን እውን ለማድረግም እንደ ሲስኮ (Cisco)፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft)፣ እና ኦራክል (Oracle) ያሉ አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቶች
የአለም አቀፍ ፓስፖርት
እንደሆኑ ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂ ለውጥ ከምንጊዜውም በላይ የፈጠነ መሆኑን የገለጹት አሰልጣኝ አቤንኤዘር፣ በተለይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ትምህርት፣ ንግድ፣ እና ጤናን በመሰሉ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አስረድተዋል። "ለውጡ አሁን እየተከሰተ ነው" ያሉት ባለሙያው፣ ኢትዮጵያም ከዚህ የቴክኖሎጂ ማዕበል ተጠቃሚ እንድትሆን ወጣቶቿን አዳዲስ ክህሎቶች በማስታጠቅ ማዘጋጀት አለባት ብለዋል።




.