Announcement የድል ዜና!

የድል ዜና!

01st August, 2025

ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ፣ "ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል። በዚህም መሠረት ኮሌጃችን ባስመዘገበው የላቀ ውጤት ሽልማት አግኝቷል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ እንዳሉት ቢሮው በ2016 የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች በ2017 በማጠናከር ስኬታማ ሥራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል። በዚህም ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የአረንጓዴ ደረጃ ምድብ ውስጥ መግባት መቻሉን ተናግረዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በተካሄደው የKPI እና ቁልፍ ተግባራት ምዘና፣ ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከኮሌጆች  አንደኛ በመሆን የክሪስታል ዋንጫ፣ ሰርተፍኬት እና የዴስክቶፕ ኮምፒውተር ተሸልሟል።

የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተኩ ታዬ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉት ዲኖች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ አስተባባሪዎች፣ ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። በተጨማሪም፣ ኮሌጁ በቀጣይ በ2018 በጀት ዓመት ይህንን ስኬት ለማስቀጠል አብሮ ለመስራት ቃል ገብቷል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with