በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የሥራ ትስስር መድረክ (Job Fair) ተካሄደ
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት (GIZ) ጋር በመተባበር ጥቅምት 27, 2018 ዓ.ም. ለሰልጣኞቹ የሥራ ትስስር መድረክ (Job Fair) በኮሌጁ ግቢ ውስጥ አካሄደ።
የመድረኩ ዋና ዓላማ ላለፉት ስድስት ወራት በኮሌጁ ሲሰለጥኑ የቆዩ ሰልጣኞችን ከተለያዩ ቀጣሪ ድርጅቶች እና ኢንዱስትሪዎች ጋር በቀጥታ በማገናኘት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
በሥራ ትስስር መድረኩ ላይ የተሳተፉት ሰልጣኞች በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፦ኮንስትራክሽን፣አውቶሞቲቭ፣ሆቴልና ቱሪዝም፣ጋርመንትና ጨርቃ ጨርቅ፣የፈርኒቸር ሥራ እና የቆዳ ውጤቶች ማምረት ይገኙበታል።
መሰል የሥራ ትስስር መድረኮች ብቁ የሰለጠነ የሰው ኃይልን ለኢንዱስትሪው ከማቅረብ ባለፈ በወጣቶች ዘንድ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ተገልጿል።


.