Announcement የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ

15th July, 2025

ሐሙስ፡- ሐምሌ  4 ቀን 2017 ዓ.ም 

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫ ውይይት አካሄደ::

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ መላው ሰራተኞቹን ባሳተፈ መድረክ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ገምግሞ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርጓል።

በዚሁ ጊዜ የኮሌጁ አመራሮች በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ማለትም የስልጠና ሂደትን፣ የተቋማዊ ሪፎርም ትግበራን እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የያዘ ሪፖርት አቅርበዋል።

በተጨማሪም በውይይቱ ላይ የተገኙ ሰራተኞች ከተቋሙ ቀጣይ እቅዶች እና ከአሰራር ማሻሻያዎች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው ከአመራሩ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።

በመጨረሻም፣ እያንዳንዱ ሰራተኛ በተቀናጀና በተነሳሽነት መንፈስ በመስራት የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት የበኩሉን እንዲወጣ አቅጣጫ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with