በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመንግስት ሰራተኞችን የፐርሶኔል መረጃ ቬሪፊኬሽን (ቆጠራ) በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።
መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ቆጠራ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስታስቲክስ አገልግሎት በተመደቡ ሦስት ባለሙያዎች አማካኝነት እስካሁን 202 አሰልጣኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ተመዝግበዋል።
የምዝገባ ሂደቱ በኮሌጁ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት እና በዋና ዲኑ የቅርብ ክትትል እየተመራ ይገኛል። በሂደቱም አንዳንድ የምዝገባውን አላማ በተመለከተ ከሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች፤ ከስታስቲክስ አገልግሎት በመጡ ባለሙያዎችና በሰው ሀብት ባለሙያዎች በቂ ማብራሪያ ተሰጥቶ ምዝገባው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑ ተመላክቷል።
የኮሌጁ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ሥንታየሁ ታምሩ እንደገለጹት፤ ቆጠራውን በተቀመጠለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ቅዳሜን ጨምሮ ስራዎች እየተሰሩ ነው። አንዳንድ የስራ መደቦች ላይ ያልተመዘገበ መረጃ በማጋጠሙም ከፐብሊክ ሰርቪስ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር መፍትሄ እየተሰጠው መሆኑን አስረድተዋል።
ዳይሬክተሯ በወጣው ፕሮግራም መሰረት እየመጡ ለተመዘገቡ ሰራተኞች ምስጋና አቅርበው፤ እስካሁን ያልተመዘገቡ ቀሪ ሰራተኞች የፋይዳ (Fayda) እና የመስሪያ ቤት መታወቂያቸውን በመያዝ በተመደበላቸው ፕሮግራም መሰረት እንዲመዘገቡ አሳስበዋል።


.