Home በ16ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በፋሽን ዲዛይን የዋንጫ አሸናፊ ሆነ

በ16ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በፋሽን ዲዛይን የዋንጫ አሸናፊ ሆነ

16th July, 2026

ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ16ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በፋሽን ዲዛይን የዋንጫ አሸናፊ ሆነ

"የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው 16ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዓውደ-ርዕይ፤ የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በፋሽን ዲዛይን ዘርፍ ከአዲስ አበባ ኮሌጆች አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።

በዓውደ-ርዕዩ ላይ የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የፋሽን ዲዛይን ሰልጣኞች ደማቅ የፋሽን ሾው ትርኢት ያቀረቡ ሲሆን፣ ተቋሙ በዘርፉ ያለውን የላቀ የፈጠራ አቅምና ተግባራዊ ክህሎት በተጨባጭ አስመስክረዋል።

የሰልጣኞቹ የፋሽን ሾው ትርኢት በተለይም የሀገር በቀል ባህላዊ ጨርቃጨርቅን ከዘመናዊ ዲዛይን ጋር አዋህዶ ያቀረበበት መንገድ ከተሳታፊዎች እና ከዳኞች ከፍተኛ አድናቆትን አትርፎለታል።

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ተኩ ታዬ ኮሌጁ ላስመዘገበው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው፤ "የዚህ አውደ-ርዕይ አላማ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን ማበረታታት፣ የሰልጣኞችን ችሎታ ማጉላትና ወጣቶች በስራ ገበያው ላይ ከፍተኛ ተፈላጊ እንዲሆኑ ማስቻል ነው" ብለዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with