ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በስነምግባር እና ፀረ ሙስና ዙሪያ ያዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አጠናቀቀ
በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከመጋቢት 7 እስከ 9, 2018 ዓ.ም. ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ስልጠናው በፌደራል የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የአውታረ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ተሾመ ጎዴቦ የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ በሰራተኞችና በአመራሩ ዘንድ የሙስናን አስከፊነት በማሳየት፣ የመልካም ስነምግባር ባህልን በማጎልበት እና ግልጸኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራርን በመተግበር የተቋሙን ራዕይ ማሳካት ነው።
አቶ ተሾመ በሰጡት ስልጠና ላይ "ሙስናን መዋጋት የሚጀምረው ከግለሰብ ራስን ከመፈተሽ ነው፤ እያንዳንዱ ሰራተኛ የተቋሙን ሀብት እንደራሱ ንብረት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም በተለያዩ ርዕሶች ላይ ጥያቄዎችን በማንሳትና ሀሳቦችን በማቅረብ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ይህ ስልጠና በኮሌጁ ውስጥ ያለውን የአሰራር ግልጸኝነት ለማሻሻል እና የሙስና ተጋላጭነትን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።



.