Home በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በታላቅ የቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት ተደረገ

በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በታላቅ የቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት ተደረገ

16th July, 2026

በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በታላቅ የቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት ተደረገ

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ "የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልጽግና" በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ (TVET) ሳምንት፤ የአሰልጣኞችን እና የሰልጣኞችን የጋራ የፈጠራ አቅም ባሳየ ደማቅ ዓውደ ርዕይ እና ጥልቅ የምክክር መድረክ አከበረ።

ይህ ከተማ አቀፍ መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኮሌጅ ዲኖች፣የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በይፋዊ የሪባን ቆረጣ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተከፍቷል።

ከኤግዚቢሽኑ በተጨማሪ ጥልቅ የፓናል ውይይት የታጀበ ነበር።የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን አቶ እንድሪስ መሐመድ፤ "የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለኢንዱስትሪ ሽግግር፡ ታሪካዊ ጉዞ፣ ወቅታዊ የሪፎርም ስኬቶች እና የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች" በሚል ርዕስ ሰፊ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል::

.

Copyright © All rights reserved.

Created with