ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም
በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ተቋማዊ የሙያ ብቃት ምዘና ተጀመረ
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ለመመዘን ተቋማዊ ሞዴል ምዘና መስጠት ጀመረ። ይህ ምዘና በተለያዩ ዲፓርትመንቶች የሚገኙ ተማሪዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ጋርመንት፣ አውቶ መካኒክ እና ኤሌክትሪክ፣ ሆቴል፣ ቢዝነስ እና አይሲቲ (ICT) ዲፓርትመንቶች ይገኙበታል።
ሰልጣኞቹ ይህንን ተቋማዊ ሞዴል ምዘና በማጠናቀቅ፣ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከል ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ዝግጅት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
በኮሌጁ እየተሰጠ ያለው ምዘና የፅንሰ ሀሳብ እና የተግባር ሲሆን፣ የፅንሰ ሀሳቡ ምዘና በonline እየተሰጠ ይገኛል።
በኮሌጁ የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሆኑት አቶ እንድሪስ መሐመድ እንደገለጹት፣ የተቋማዊ ምዘናው ዋና ዓላማ ሰልጣኞች ለሀገር አቀፉ የብቃት ምዘና ከመቅረባቸው በፊት ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ለመፈተሽ እንዲሁም ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ነው።
የ2017 ተመራቂ ሰልጣኞች ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚመረቁ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሰልጣኞች መመረቅ የሚችሉት የሙያ ብቃታቸውን ሲያረጋግጡ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።








.